ለግላዊነት ያለን አቀራረብ

  በመረጃ ግላዊነት አንቀጽ ህግ/Information Privacy Act 2000 (Vic) በወጣው የመረጃ ግላዊነት ስራአት መሰረት የርስዎ ግላዊ የሆነ መረጃን በአግባቡና ሃላፊነት ባለው መልኩ ለማስተናገድእንዳለበት የተከራዮች ማሕበር ህጋዊ አገልግሎት ቃል ይገባል።

  በዚህ የግላዊነት ጽሁፋዊ መግለጫ ላይ ምን ዓይነት መረጃ ከርስዎ እንደሚወሰድ እና እንዴት አድርገን መጠቀም እና መረጃዎን ለሌላ አካል ማውጣት እንዳለብን፤ ያለዎትን መረጃ ለመጠቀም እቀባ ማድረግና ለሌላ እንደሚወጣ ፍላጎትዎንና የርስዎን ግላዊነት ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ እንዳስቀመጥን ያለን አሰራር እንዴት አድርገው መመሪያ መስጠት እንደሚችሉ ይሆናል። በእኛ የደንበኛ ሚስጢራዊነት ግዴታ ያለው መረጃ በዚህ ግላዊነት ፖሊሲ ውስጥ እንዳልተጠቀሰ ነገር ግን በእኛ የእርዳታ ሁኔታ/Conditions of Assistance ላይ ተገልጿል።

  ‘የግላዊነት መረጃ’ ትርጉም

  ግላዊነት መረጃ ማለት ስለግለሰቡ ያለ መረጃ ወይም ፍላጎት ነው። ከምንሰበስበው ግላዊ የሆነ መረጃ ውስጥ የሚካተት፤ ስም፣ አድራሻ፣ ተለፎንና ኢሜል ዝርዝር መረጃ፣ ዝርዝር ቅሬታ እና ለርስዎ በምናካሂደው የሥራ ተግባር ላይ ጠቃሚ የሆነ መረጃ ይሆናል።

  የርስዎ ስምምነት

  በዚህ ድረገጽ ወይም በሌላ በኩል ስለርስዎ መረጃ ለእኛ በማቅረብ ማለት፤ በዚህ ግላዊነት ፖሊሲ በወጣው መሰረት የርስዎን መረጃ ለመሰብሰብ፣ ለመጠቀም፣ ለሌላ አሳልፎ ለማውጣት እና ለማስተላለፍ ፈቃድ እንደተስማሙ ነው።

  ይህንን ግላዊነት ፖሊሲ ከቀየርን ያሉትን ለውጦች በዚህ ድረገጽ አድርገን እንደምንልክና በዚህ ድረገጽ ባለው ገጽ ጀርባ ላይ ማሳሰቢያ ማስቀመጥ እንችል ይሆናል፤ ስለዚህ እንዴት መረጃ መሰብሰብ እንዳለብን እና በማንኛውም ጊዜ እንዴት መጠቀም እንዳለብን ማወቅ ይችላሉ። መረጃ በዚህ ድረገጽ ላይ እንደደረሰ ወዲያውኑ ለውጦቱ ተግባራዊ ይሆናሉ።

  ስለርስዎ የምንሰበስበው መረጃ እና እንዴት አድርገን መጠቀምና ወደሌላ ማውጣት እንደምንችል

  ብዛት ባለቸው ሁኔታዎች ላይ ስለርስዎ መረጃ መሰብሰብ እንችል ይሆናል፤ በዚህ ውስጥ የሚካተት ህጋዊ የሆነ እርዳታ እና ምክር ከእኛ ሲፈልጉ፤ በማንኛውም የድረገጽ ላይ ጥያቄ ሲያቀርቡ፤ ስልጠናን ያካተተ ሰሚናር ስብሰባ ወይም በሌላ ድርጊት ላይ በሚሳተፉበት ጊዜ፤ በእኛ ስላለ ሥራ ሲያመለክቱ ወይም ለሥራው ተቀባይነት በሚሰጡበት ጊዜ ከእኛ መረጃ ለማግኘት በሚፈርሙበት ጊዜ፤ ወይም ለእኛ አገልግሎት እንዲሰጡ በሚቀርብልዎት ጊዜ ይሆናል።

  ስለርስዎ ያለን መረጃ በህገወጥነት፣ ያለምክንያት ጣልቃ በመግባት ወይም በግዳጅነት የመሰብሰብ መንገዶችን አንጠቀምም።

  እኛ በምንሰበስበው መረጃ ላይ የሚካተት እንደ የርስዎ ስም፣ የመልእክት አድራሻ፣ ኢሜል አድራሻ፣ ተለፎን ቁጥር እና ስለርስዎ ሥራ በተመለከተ መረጃ፣ የርስዎ ገቢ መጠን እና/ወይም እርስዎ የሚፈልጉት ሌላ መረጃ ወይም እርስዎ ለመረጡት ህጋዊ የሆነ አገልግሎት የምናቀብበት ቦታ ይሆናል። ጊዜ እየጨመረ ሲሄድ ስለርስዎ ጤና መረጃ እና ስለማንኛውም የፈጸሙት ወንጀል ሪኮርድ ዝርዝር መረጃን ሊያካትት ይችላል።

  ጊዜ እየጨመረ ሲሄድ በእኛ የሚያስፈልግን መረጃ ካላቀረቡ፤ ለርስዎ የሚሆን አገልግሎት ልናቀርብልዎ አንችልም ወይም ያቀረብንልዎ የመረጃ ጥያቄ መሟላት እንዳለበት ነው።

  ህጋዊ ለሆነ ወይም ተመሳሳይ ለሆነ ማመልከቻ ወይም ሚስጢራዊ በሆነ የክርክር መፍትሄ ማስገኛ አሰራር ለማቀናጀት፣ ለመሟገት ወይም ለመከላከል ሲባል ላለዎት ግላዊ ጥሬ መረጃ አስፈላጊ ከሆነ መውሰድ፣ መጠቀምና ለሌላ አሳልፈን መስጠት እንችል ይሆናል።

  ስለ እኛ አገልግሎቶችና ደንበኞች የተገኘን መረጃ በተመለከተ ሁልጌዜ ለቪክቶሪያ አስተዳደር ግዛትና ለኮመንዌልዝ መንግሥታት ለሁለቱም ሪፖርት ማድረግ አለብን። ከእኛ ተከታታይ የሆነ ህጋዊ ምክርና እርዳታ ከፈለጉ፤ ከዚህ የሚከተሉትም መረጃዎች በማቅረብ እንዲረዱን እንጠይቃለን:

  • የጾታ ዓይነት
  • እራስዎ እንደ የአገር ተወላጅ ስለመሆን you identify as Indigenous
  • በአካል ጉዳተኛነት የሚሰቃዩ ከሆነ
  • የገቢ መጠንዎ ገደብና ምንጩ
  • አስተርጓሚ ካስፈለግዎ
  • የሲንተርሊንክ/Centrelink ጡሮታ ወይም የገቢ ድጋፍ ክፍያን የሚያገኙ ከሆነ።

  በቀጣይነት ከእኛ ህጋዊ እርዳታ ስለማግኘት ጉዳይ በሚኖረን የስምምነት ሁኔታ መሰረት ያተኮረ ነው። እንዲሁም ግላዊ የሆነ መረጃ የምንሰበስበው ለ :

  • ከእኛ ስለሚፈቀድልዎ ህጋዊ የሆነ እርዳታ ግምገማ ለማካሄድ
  • ህጋዊ የሆነ እርዳታን በሚያቀርቡ ሰራተኞች ላይ ግምገማ ለማካሄድ
  • በህጋዊ የሙያተኛ ስነ-ምግባር እና ህጋዊነት ላይ የምናካሂደውን ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ ይሆናል። .

  በቪክቶሪያ የተከራዮች ማሕበር ባለው የማህበራዊ አሰራር ክፍል በወጣው መሰረት ለብዙሀን መገናኛ እና ለጽሁፋዊ ህትመቶች በሚል ዓላማ ጠቅለል ያለ መረጃ እና ስታስቲክስ መጠቀም እንችል ይሆናል።

  በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ስለርስዎ ግላዊ የሆነ መረጃ ከሶስተኛ አካል ምንጭ እንወስዳለን። ለምሳሌ፡ እርስዎ በሚደራደሩት ከሌላ ድርጅቶች፣ ከመንግሥታዊ ድርጅቶች፣ እና ከመረጃ ወይም አገልግሎት አቅራቢዎች ወይም ለህዝባዊ ከቀረበ ሪኮርድ ላይ ግላዊ የሆኑ መረጃዎችን መሰብሰብ እንችል ይሆናል።

  ህጋዊ የሆነ ምክር፣ እርዳታና መረጃ ለመስጠት፤ በዜና ላይ፤ በህትመት፣ ሰሚናር ላይ እና በድርጊስት ፍጻሜ ላይ ለማቅረብ፤ ለርስዎ የሚቀርበውን አገልግሎትና ግንኙነት ለማጠናከር፤ ለእኛ የጠየቁትንና ማመልከቻዎን በአሰራር ሂደት ለመፈጸም፤ እንዲሁም ከዚህ በላይ ለተጠቀሰው ማንኛውም ጉዳይ በተዛመደ በሚል ያለንን መረጃ ለርስዎ ለመላክ ሲባል ከርስዎ የተወሰደን ማንኛውም መረጃ እኛ፣ የእኛ ሠራተኞች፣ ተወካዮች፣ አማካሪዎች እና በኮንትራት ስር ተቀጥረው የሚሰሩ ሰዎች መጠቀም ይችሉ ይሆናል። እንዲሁ በህጉ መሰረት ከተፈቀደልን ግላዊ የሆነ መረጃ ወይም ጥሬ መረጃን መጠቀም እንችል ይሆናል። ይህንን ለመጠቀም በስምምነት ከገለጹ በዚህ ሁኔታ ላይ ይካተታል።

  የርስዎን ግላዊ መረጃ በሚከተለው ሁኔታ ወደሌላ አሳልፎ መስጠት እንችል ይሆናል:

  • እርስዎ የተከራዮች ማሕበር ህጋዊ የሆነ አገልግሎት ደንበኛ ከሆኑ ያለዎትን ግላዊ መረጃ ለሚከተለው አሳልፈን መስጠት እንችል ይሆናል:
   • ለአንጋፋ የህግ ጠበቃ፤ ለሌላ ልዩ የህጋዊ ሙያተኞች (አስታራቂዎችን ያካተተ)፤ በርስዎ ጉዳይ ላይ ተሳትፎ ያላቸው አማካሪዎች ወይም ኤክስፐርቶች፤ ወይም
   • በበለጠ ህጋዊ የሆነ ምክር ወይም ሌላ ዓይነት እርዳታ እንዲያገኙ ሌላ የማህበረሰብ ህጋዊ የሆነ አገልግሎቶች ወይም የማህበራዊ እና በጎ አድራጎት አገልግሎት አቅራቢዎች።
  • ለማንኛውም የእኛ ደንበኞች ህጋዊ የሆነ አገልግሎት በሚቀርብበት ጊዜ የርስዎን ግላዊ መረጃ ተወስዶ ከሆነ ታዲያ እነዚህን አገልግሎቶች በሎች ለማቅረብ ሲባል በህጉ መሰረት ፈቃድ ከተሰጠ መረጃን ለዚያ ደንበኛ አሳልፎ መስጠት እንችል ይሆናል;
  • ድርጅታችን እንዲካሄድ ለሚረዱ የእኛ ሠራተኞች፣ ተወካዮች፣ አማካሪዎች እና በኮንትራት ስር ተቀጥረው ለሚሰሩ ሰዎች የርስዎን ግላዊ መረጃ መስጠት ስንችል፤ ይህም በድረገጽ፣ ወይም በተዛመደ አገልግሎት ያካተተ ሲሆን በእኛ የደህንነትና ሚስጢራዊነት ጥበቃ ግዴታ ላሟላ ሲሆን፤ እንዲሁም
  • የርስዎን ግላዊ መረጃ አሳልፈን መስጠት የሚቻለው ህጉ በሚጠይቀው መሰረት ወይም ይህን ለማድረግ ፈቃድ ካገኘን ነው።

  ስለ ሌላ ሰዎች መረጃ ለእኛ የሰጡት

  ስለ አንድ ሰው ግላዊ መረጃ ለእኛ ከሰጡ (ማለት እንደ ተወካይ ዘመድ ወይም ጓደኛ ሆኖ እርዳታ ሲፈልጉ) ለእኛ ያንን መረጃ አውጥቶ ስለመስጠት እርግጠኛ መሆን አለብዎ፤ ይህም በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ በተገለጸው መረጃ መሰረት እኛ የሆነ እርምጃዎች ሳንወስድ፤ መረጃውን መሰብሰብ፣ መጠቀምና አሳልፎ ለሌላ መስጠት እንችል ይሆናል። በተለይ በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ በተዘረዘረው የተለያዩ ጉዳዮች መሰረት በግለሰቡ ያለን አሳሳቢ ሁኔታ ስለማወቅዎ ማረጋገጥ አለብዎት፤ እነዚህም በዚያ ግለሰብ የተዛመዱ ጉዳዮች ማለት የእኛን ማንነት፣ እንዴት እኛን ማነጋገር እንደሚቻል፣ የምንሰበስብበት ዓላማ፣ የእኛ መረጃ ስለመውጣት ልምድ (ለውጭ አገር ተጠቃሚዎች አውጥቶ መስጠትን ያካተተ) ሲሆን ለመረጃው አግንቶ ስለመጠቀምና በመረጃው አያያዝ ላይ ቅሬታ ለማቅረብ የግለሰቡ መብት እና መረጃው ካልቀረበ የሚያስከትለው ሰበብ (ማለት እንደ አገልግሎቶችን ማቅረብ አለመቻል)።

  ለርስዎ ደህንነት መረጃን ስለመጠበቅ

  የርስዎን መረጃ በሚስጢራዊነት ለመጠበቅ እና እንዳይጠፋ ለመጠበቅ፤ አላግባብ መጠቀምና ፈቃድ ባለው ለመጠቀም እንዲቻል ተገቢ የሆነ ተክኒካል አቀራረብ እና ድርጅታዊ እርምጃ እንወስዳለን። ያለን መረጃ በእኛ የመረጃ ተክኖሎጂ አሰራር ዘዴዎች ወይም በወረቀት ፋይሎች ላይ ሊቀመጥ ይችላል።

  የርስዎን መረጃ አስፈላጊ ከሆነበት በላይ ለረጂም ጊዜ አናስቀምጥም።

  ስለርስዎ ያለን መረጃ ወቅታዊ ስለማድረግ

  ከሰጡን መረጃዎች የሆኑ ለውጦች ካሉ፤ ልምሳሌ፡ የርስዎን ኢሜል አድራሻ ከቀየሩ ወይም ለእኛ ካቀረቡት ጥያቄ ላይ መሰረዝ የሚፈልጉት ካለ፤ እባክዎ በኢሜል አድርገው ወደ admin@tuv.org.au በመላክ ያሳውቁን።

  የርስዎ መብቶች

  በእኛ ስላለው የርስዎ ግላዊ የሆነ መረጃ ቅጂውን ለመጠየቅ፤ ትክክለኛ ስላልሆነ ግላዊ መረጃ ለማረም እና የእርስዎን ግላዊ የሆነ መረጃ ለመገባበያ በሚል ዓላማ ስለመጠቀማችን ተቃውሞ ለማቅረብ መብት አለዎት። እንዲሁም የርስዎን ግላዊ መረጃ አያያዝ ላይ በእኛ ላይ ደስተኛ ካልሆኑ ቅሬታ ማቅረብ ይችሉ ይሆናል።

  ከዚህ በላይ ባለው በማንኛውም ማካሄድ ከፈለጉ፤ እባክዎ በኢሜል አድርገው ወደ admin@tuv.org.au ይላኩ።

  እንዲሁም በስልክ 03 9411 1444 አድርጎ መደውል እንደሚችሉና ለህጋዊ የሆነ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ለማነጋገር መጠየቅ።

  እኛ ለደረሰን ማንኛውም ቅሬታ ግምት ውስጥ እንደምናስገባና በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ (በአብዛኛው እንደደረሰ በ 30 ቀናት ውስጥ) ምላሽ እንሰጥዎታለን። በምናቀርብልዎት ምላሽ ደስተኛ ካልሆኑ ያለዎትን ቅሬታ ወደ ጠቃሚ የሆነ ግላዊነት ተቆጣጣሪ መውሰድ ይችሉ ይሆናል። ለርስዎ ጠቃሚ የሆነ ተቆጣጣሪ ዝርዝር መረጃ ከጠየቁ እናቀርብልዎታለን።

  እኛን እንዴት ማነጋገር እንደሚቻል

  ስለ እኛ ድረገጽ እና የእኛ ግላዊነት ፖሊሲ አስተያየትዎን እንቀበላለን። ከማንኛውም ጥያቄዎች ወይም አስተያየቶች ጋር በተዛመደ እኛን ማነጋገር ከፈለጉ፤ እባክዎ በኢሜል አድርገው ወደ admin@tuv.org.au መላክ ወይም ደብዳቤ ወደ ህጋዊ የሆነ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ፣ በቪክቶሪያ የተከራዮች ማሕበር/Tenants Union of Victoria/Tenants Victoria, በአድራሻ ፖ.ሳ.ቁጥር 234, FITZROY, VIC 3065 አድርገው ይላኩት።

   


  Our approach to privacy | Amharic

  Tenants Victoria acknowledges the support of the Victorian Government.