ለተከራዮች የእርዳታ መስመር: (03) 9416 2577

  በተከራዮች የእርዳታ መስመር በኩል ሚስጢራዊና ያለክፍያ በነጻ መረጃና የምክር አገልግሎት ይቀርባል። 03 9416 2577

  የእኛን አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ ስለሚኖርዎ ግላዊነት መረጃ ለህጋዊ የሆነ አገልግሎት ግላዊነት ፖሊሲ/Legal Service Privacy Policy የሚለውን ማየት።

  የእኛን አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ ስለሚያካሂዱት መደበኛ ስምምነት መረጃ በእኛ የደንበኛ አገልግሎት መመሪያ ላይ ማየት።

  ማንን እንደምንረዳ

  በቪክቶሪያ ውስጥ የመኖሪያ መጠለያ ተከራይተው ለሚኖሩና ቤት ተከራዮች እንረዳለን።
  ባለንብረቶችን ወይም የንብረት ተወካዮችን አንረዳም። ባለንብረቱ ምክር ለማግኘት በቪክቶሪያ ለተጠቃሚ ጉዳይ በስልክ 1300 55 81 81መደወል ይቻላል።

  በምን መልኩ ልንረዳዎ እንደምንችል

  ከባልንብረቶች፣ ክንብረት ተወካዮች እና ከአንዳንድ የተከራይና አከራይ ጉዳዮች ከቤተሰብ ሁከት ፈጠራ ጋር በተዛመደ ስለሚኖሩ ችግሮች መሰረታዊ ምክርና መረጃ በተከራዮች የእርዳታ መስመር ላይ ማቅረብ እንችላለን።
  በተከራዮች እና በጎረቤታሞች መካከል ባሉ ችግሮች ላይ ምክር አንሰጥም፤ ነገር ግን የርስዎን በአካባቢዎ ያለን የማህበረሰብ ህጋዊ የሆነ ማእከል ማነጋገር ይችላሉ።

  ለመረጃ እና መሰረታዊ ምክር ብቻ

  ጥሪዎችዎ በተቻለ መጠን አጭር እንዲሆን ለመርዳት እንሞክራለን ነገር ግን ለጥያቄዎ ትክክለኛ ምላሽ ለመስጠት በቂ ጊዜ እንመድባለን. በአጠቃላይ, ጥሪዎች ከ5-10 ደቂቃዎች ይወስዳሉ. ምክሮቻችን መረጃዎችን እና መሠረታዊ ምክሮችን በስልክ ብቻ መስጠት ይችላሉ. የርስዎ የተከራይና አከራይ ችግር ውስብስብ ከሆነ, እኛን ለማየት ለእኛ ቀጠሮ ልንይዝ እንችላለን።

  ከፍተኛ ጥያቄ

  የእኛን ስልክ አገልግሎት ለማግኘት ከፍተኛ ጥያቄ እንዳለና ታዲያ የርስዎን ጥሪ ወዲያውኑ መመለስ አንችል ይሆናል። የርስዎ ጥሪ ተራ እንደሚጠብቅና በተቻለ ፍጥነት ምላሽ ይሰጣል ነገር ግን እባክዎ ያስተውሉ፤ የስልክ ጥሪ በበዛበት ጊዜ እስከ 20 ደቂቃዎች ወይም ከዚያም በላይ ማስጠበቅ እንደሚችል ነው። ተይዣለሁ የሚል ምልክት ከሰሙ ይህም የጥሪ ተራ መጠበቁ ሞልቷል ማለት ሲሆን ቆይተው መሞከር ይችላሉ። የእርስዎ ትእግስት የሚደነቅ ነው።

  ረጂም ጥበቃን ማስወገድ

  የርስዎ ጥያቄ በድረገጻችን ላይ መልስ ተሰጥቶበት ይሆናል። አጠቃላይ ህጋዊ የሆኑ መረጃዎችን ብዛት ባለው በመደበኛ የተከራይና አከራይ አርእስቶች ላይ ማግኘት ሲችሉ እንዲሁም በእውነታ ጽሁፋዊ ወረቀትና ደረጃ በደረጃ መመሪያዎች፡ ምክርበሚለው ላይ ማግኘት ይችላሉ።

  ከመደወልዎ በፊት

  የመክፈቻና መዝጊያ ጊዚያት ማጣራትዎን ማረጋገጥና ከዚህ በታች ያሉትን ነገሮዎች ማዘጋጀት:

  • እስክብሪቶና ወረቀት
  • የርስዎን ባለንብረትና የንብረት ተወካይ ስም
  • ጠቃሚ የሆኑ ሰነዶችን፤ ይህም የርስዎን ተከራይና አከራይ ስምምነት፣ ለተሰጥዎ ማንኛውም ማስጠንቀቂያ ማለት ከርስዎ ባለንብረት ወይም ከንብረት ተወካይ እንደ የቤት ማስለቀቂያ ማስጠንቀቂያና የሆነ ደብዳቤ ወይም ቅጽ ደርስዎት ከሆነ ነው።

  መቸ ነው ስልክ የሚደወል

  ሰኞ9.00 am እስከ 4.00 pm
  ማክሰኞ9.00 am እስከ 4.00 pm
  ረቡዕ9:00 am እስከ 4.00 pm
  ሐሙስ9.00 am እስከ 4.00 pm
  ዓርብ9.00 am እስከ 4.00 pm

  ለተከራዮች የእርዳታ መስመር በህዝባዊ በዓላት ቀኖች ላይ ዝግ ነው


  Helpline | Amharic

  Tenants Victoria acknowledges the support of the Victorian Government.