ባለንብረቱ ቤቱን ስለመሸጥ - Tenants Victoria

ባለንብረቱ ቤቱን ስለመሸጥ

ምንም እንኳን የተወሰነ የአከራይና ተከራይ ስምምነት ውል ቢኖርዎም ባለንብረቱ ቤቱን መሸጥ እንደሚችል ነው። ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ቤቱን ሲሸጡ የተከራይና አከራይ ውል ህግን መከተል አለባቸው።

ይህ ገጽ

ቤቱን ስለማሳየትና መጐብኘት
ማስታወቂያ ስለመለጠፍ
ለስምምነት ስለመደራደር
ያላግባብ ወይም በህገ-ወጥነት መግባት
ባለንብረቱ ቤቱን ሲሸጥ ስለመልቀቅ
የማስያዣ ገንዘብ

ቤቱን ስለማሳየትና መጐብኘት

ባለንብረቱ በተገቢው ማሳሰቢያ ከሰጥዎት ወደ ንብረቱ መግዛት ለፈለጉ ሰዎች ለማሳየት መብት እንዳለውና ተከራዩም ወደ ቤት እንዲገቡ መፍቀድ ግዴታው ይሆናል። ስለዚህ የተከራዩ መብትን ማለት ጎብኚ በሚመጣበት ጊዜ ‘በተከራየው ቤት ጸጥታን’ ማረጋገጥ የባለንብረቱ ሃላፊነት ይሆናል።

እርስዎ ከተስማሙ ባለንብረቱ ወደ ቤት ውስጥ መግባት ሲችል ይህም መግባት ከተፈለገበት ጊዜ በ7 ቀናት ውስጥ ማሳወቅ። በዚህ ከተስማሙ ምንም እንኳን በተክስት ወይም በኢሜል ቢሆንም በጽሁፍ አድርጎ ማስቀመጡ ጥሩ ነው።

በሚኖሩበት ቤት ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ መግባት ከፈለጉና እርስዎ ካልተስማሙበት፣ ማድረግ ያለባቸው:

  • መጎብኘት የፈለጉበትን ምክንያት የሚገልጽ ጽሁፋዊ ማሳሰቢያ ቢያንስ በ24 ሰዓታት ለርስዎ መስጠት
  • ከጥዋቱ 8am እና ከሰዓት በኋላ 6pm ባለው ጊዜ ውስጥ ማሳሰቢያውን በአካል ለርስዎ መስጠት ወይም በፖስታ መላክ
  • ከጥዋቱ 8am እስከ ከሰዓት በኋላ 6pm ባለው ጊዜ ብቻ መጎብኘት እንጂ በህዝብ በዓላት ጊዜ አይደለም (ባለፊት 7 ቀናት ውስጥ ካልተስማሙ በስተቀር)
  • ካስፈላጊው ጊዜ በላይ አለመቆየት።

የሚቀርበው ምክንያት በተከራዮች ህግ ውስጥ ባለው አንደኛው ምክንያት መሆን አለበት። ለምሳሌ፡ ባለንብረቱ ቤቱን የሚሸጥ ከሆነ ለመግባት የሚሰጠው ምክንያት የቤቱን ዋጋ ለማስገመት ወይም ቤቱን ለሚገዙ ሰዎች ለማሳየት ይሆናል።

ማሳሰቢያው በመደበኛ ፖስታ መልእክት ከተላከ፤ እስከሚደርስ ተጨማሪ የአንድ ሥራ ቀን መፈቀድ አለበት። ማሳሰቢያው የተላከው በተመዘገበ ፖስታ መልእክት ከሆነ እስኪደርስ ድረስ የሁለት የሥራ ቀናት መጨመር አለባቸው።

ባለንብረቱ ተገቢ የሆነ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ከሆነ ተከራዩ ቢስማማም ባይስማማ እንዲሁም ጉብኝት በሚደረግበት ጊዜ ቤት ቢኖሩም ባይኖሩም ለመግባት አስፈላጊ ከሆነ ማንኛውም ሰው ጋር ሆኖ ወደ ቤት እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል (ይህም እንደ ንብረት ተወካይ፣ ዋጋ ገማች ወይም ለመግዛት ፈላጊ ሰው ማስገባት)።

በተገቢው ማሳሰቢያ ካልደረስዎት፤ ለነሱም ሆነ ቤቱን መግዛት ለፈለገ ሰው ወደ ቤት ውስጥ አለማስገባት ይችላሉ።

ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ በቂ ምክንያት ከሌላቸው በስተቀር የመግቢያ ቅድመ ሁኔታን ሳያሟሉ ወደ ቤት መግባቱ ወንጀል ነው።

ማስታወቂያ ስለመለጠፍ

ንብረቱን ለሚገዙ ማሳየቱ እንደ አንደኛው ሂደት ሲሆን ታዲያ የንብረቱን ውስጣዊ ገጽታ በፎቶግራፍ ተደርጎ የሚሸጥ በሚል ሰሌዳ ላይና በኢንተርኔት ላይ ማስታወቂያ ይወጣል።

ቤቱን ለመሸጥ ለማስታወቂያ የሚሆን ፎቶግራፍ ለማንሳት ባለንብረቱ ወደ ቤት ውስጥ የመግባት መብት የለውም ታዲያ ለዚህ ጉዳይ ወደ ቤት ለመግባት አለመፍቀድ ይችላሉ። ቤቱን ለመሸጥ ለማስታወቂያ የሚሆን ፎቶግራፍ ለማንሳት ባለንብረቱ ወደ ቤት ውስጥ ለመግባት ከፈለገ መጀመሪያ ምን ዓይነት ፎቶግራፍ እንደሚወሰድና ለምን እንደሚጠቅም ከተከራዩ ጋር ተደራድሮ ስምምነት ላይ ለመድረስ መሞከር አለበት። ፎቶግራፍ አንሺው ከባለንብረቱ ጋር ወይም ከንብረት ተወካዩ ጋር አብሮ እንዲመጣ መጠየቅ ይችላሉ።

ፎቶግራፉ በርስዎ ንብረት ላይ ለስርቆት ችግር የሚያጋልጥ ከሆነ ታዲያ ፎቶ ከመነሳቱ በፊት ማንኛውንም ጠቃሚ የሆነ እቃዎች ማውጣት አለብዎት።

የተወሰደው ፎቶግራፍ የርስዎን ግላዊነት መብት ግዴታ ይጥሳል በሚል ካሳሰብዎት ምክንያቱም እርስዎን ወይም የቤተሰብ አባልዎን በግልጽ መለየት ስለሚቻል ታዲያ ምክር ለማግኘት የፈደራል ግላዊነት ኮሚሽንን/ Federal Privacy Commissioner በስልክ  1300 363 992 ደውሎ ማነጋገር።

ለስምምነት ስለመደራደር

በተከራዩበት ቤት ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ መቸ እና በየስንት ጊዜው መግባት እንዳለባቸው ተደራድሮ መስማማት ይችሉ ይሆናል። ስምምነት ላይ ከደረሱ ታዲያ በጹሁፍ ተደርጎ በርስዎና እና በባለንብረቱ ወይም ተወካዩ እንደተፈረመበት ማረጋገጥ አለብዎ።

በስምምነቱ ላይ እንደሚከተለው ሁኔታዎችን ማካተት አለበት:

  • ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ መግዛት ለፈለገው ሰው ንብረቱን ማሳየት የሚችለው ከተከራዩ ጋር አመቺ የሆነ ጊዜ ቀጠሮ በማቀናጀት ብቻ ነው።
  • መግዛት ለፈለጉ ሰዎች ንብረቱን ለማሳየት እስከ ጨረታ ሽያጭ የሚወጣበት ቀን ወይም እስከ ተስማሙበት ቀን ቤቱ በየሳምንቱ ክፍት ይሆናል።
  • ቤቱን በማሳየት ለሚከሰት ችግር የማካካሻ ክፍያ በሚል ተከራዩ አነስተኛ የቤት ኪራይ ይከፍላል።

ያላግባብ ወይም በህገ-ወጥነት መግባት

ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ ያላግባብ ወደ ቤት የመግባት መብታቸውን ተጠቅመዋል ብለው ካመኑበት ለልዩ ፍርድ ቤት (VCAT) ማመልከት እንደሚችሉና ታዲያ በተከራዩበት ቤት ያለን ጸጥታ እንዳይረብሹ ለማድረግ የእገዳ ትእዛዝ ይሰጣቸዋል። ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ በቂ የሆነ ማሳሰቢያ ካልሰጥዎት ወይም ብዙጊዜ ወደ ንብረቱ የሚመጡ ከሆነ ታዲያ ይህ ያለምክንያት መምጣት ሊያሰኝ ይችላል።

በተከራዩበት ቤት ያለን ጸጥታ የመጠበቅ የሥራ ተግባር ባለንብረቱ መወሰድ ያለበትን ተገቢ እርጃዎች ካላሟላ ታዲያ የማካካሻ ክፍያ እንዲሰጥዎ ማመልከት ይችሉ ይሆናል። በተከራዩበት ቤት ለመግባት ባለንብረቱ ወይም የንብረት ተወካዩ ተገቢ የሆነ ማሳሰቢያ ካልሰጡ ወይም ለመግባት ያላቸውን መብት ያላግባብ ከተጠቀሙበት ያለባቸውን ግዴታ እንደጣሱ ይሆናል። የንብረት ፍተሻ በሚካሄድበት ጊዜ የርስዎ እቃዎች ከተሰረቁ ውይም ከተበላሹ የማካካሻ ክፍያ እንዲሰጥዎም መጠየቅ ይችሉ ይሆናል።

ባለንብረቱ ትክክል አይደለም ብለው ካሰቡ ስለተፈጠረው ሁኔታ በቂ ማስረጃ ማሰባሰብ ይኖርብዎታል። ለምሳሌ፡ ያካሄዱትን ሥራዎች በቀን መቁጠሪያ ላይ መመዝገብ፤ ይህም በንብረቱ ላይ ሰዎች ስንት ጊዜ እንደመጡና በእያንዳንዱ ምን ያህል ጊዜ እንደቆዩ መመዝገብ።

ንብረቱን መግዛት ለሚፈልጉ ሰዎች ንብረቱ በጥሩ ሁኔታ እንዲሆን ማንኛውንም ጥረት ወይም ወጪ (አበባዎች መግዛት ወይም ባለሙያ ጽዳት ሰራተኞች ለመቅጠር) ማውጣት ግዴታ የለብዎም። ባለንብረቱ የሚፈልገው ይህንን ከሆነ ማቀናጀቱ የራሳቸው ሀላፊነት ይሆናል። በነዋሪ ተከራዮች አንቀጽ ህግ/ Residential Tenancies Act 1997 ዓ.ም መሰረት የርስዎ ግዴታ ንብረቱን በንጽህና እንደነበረው መጠበቅ ይሆናል።፡

ባለንብረቱ ቤቱን ሲሸጥ ስለመልቀቅ

ባለንብረቱ ቤቱን ሸጠ ማለት ወዲያውኑ ይወጣሉ ማለት አይደለም። የርስዎ ተከራይና አከራይ ውል ጊዜው እስኪደርስ ድረስ ይቀጥልና በትክክለኛው የጊዜ ገደብ ያልቃል።

በወቅቱ የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ለተወሰነ የጊዜ ገደብ ካለዎት ታዲያ የጊዜ ገደቡ ከማለቁ በፊት ቤቱን መልቀቅ አይኖርብዎም። በቤት ውስጥ እያሉ ንብረቱ ከተሸጠ አዲስ የሚገዛው ሰው የርስዎን የተከራይና አከራይ ውል ግምት ውስጥ አስገብቶ ቀደም ሲል የነበረውን ባለንብረት ሃላፊነቶች ይወስዳል። ይህ ማለት ያለዎት የጊዜ ገደብና ሁኔታ ስምምነት በቀጣይነት ተግባራዊ ይሆናል (የሚከፍሉት ቤት ኪራይ መጠን፣ እንዴትና መቸ መክፈል እንዳለብዎ እና የተወሰነው ጊዜ ገደቡ የሚያልቅበትን ቀን ያካትታል)።

ባለንብረቱ ቤቱን እንዲለቁ ከፈለገ የ60 ቀናት የመልቀቂያ ማስጠንቀቂያ፣ ምክንያቱን በመግለጽ መስጠት አለባቸው (ይህም ንብረቱ የሚሸጠው ባዶ እንደሆነ ስለተደረገ)። ባለንብረቱ ለመሸጥ ኮንትራት ሲፈርም በ14 ቀናት ውስጥ ለርስዎ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለበት፤ ወይም በሽያጭ ኮንትራት ላይ ለየት ያለ ሁኔታ ካል በማያያዝ ታዲያ እነዚህ ሁኔታዎች ከተፈጸሙ በኋላ በ14 ቀናት ውስጥ ማስጠንቀቂያ ሊሰጥ ይችላል። ለተወሰነ ጊዜ ገደብ የተከራይ ስምምነት ውል ካለዎት፤ የማስጠንቀቂያው መጨረሻ ቀን ከተወሰነ ጊዜ ገደብ ውል ቀን በፊት መሆን አይችልም።

ከርስዎ የተወሰነ ጊዜ ገደብ ውል ቀን በፊት አዲሱ ባለንብረት እንዲወጡለት ከፈለገ፤ ለሚፈጠረው ችግር ማካካሻ ክፍያ እንዲሰጥ ተነጋግሮ ለመስማማት መሞከር አለብዎት። ስምምነት ላይ ከደረሱ ታዲያ በጽሁፍ ተደርጎ የርስዎና የአዲሱ ባለንብረት ወይም ተወካዩ ፊርማ ስለማካተቱ ማረጋገጥ ነው።

በተወሰነ ጊዜ ገደብ የተከራይ ስምምነት ውል ላይ ከሆኑና ንብረቱ ስለሚሸጥ ወይም ከተሸጠ ቀደም ብለው መልቀቅ ከፈለጉ ታዲያ የተከራይ ውሉ ‘በጋራ ስምምነት’ ከባለንብረቱ ጋር በማካሄድ ኩንትራቱን ማቋረጥ ይቻላል። የሚካሄደውን ስምምነት በጽሁፍ አድርጎ ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ መፈረም አለባቸው አለበለዚያ የኮንትራት ውሉን በመጣስ ሊያስከፍልዎት ይችላል።

በየጊዜው የሚታደስ ኮንትራት (በየወሩ የሚታደስ) ውል ላይ ከሆኑና የ60 ቀናት መልቀቂያ ማስጠንቀቂያ ከተሰጥዎት፤ 60 ቀናት ከመድረሱ በፊት ቤቱን መልቀቅ ይችላሉ። ይሁን እንጂ እርስዎ መልቀቅ እንደፈለጉ የ14 ቀናት መልቀቂያ ማሳሰቢያ ለባለንብረቱ ወይም ለአዲስ ገዥው መስጠት አለብዎት።

የማስያዣ ገንዘብ

ንብረቱ በሚሸጥበት ጊዜ አዲሱም ሆነ የድሮው ባለንብረት ንብረቱ ለሌላ ሰው እንደተላለፈ ለነዋሪ ተከራዮች ማስያዣ ገንዘብ ባለሥልጣን ማሳወቅ አለባቸው። ያለዎት የተከራይና አከራይ ውል እስኪያልቅ ድረስ የማስያዣ ገንዘቡ በገንዘብ ማስያዣ ባለሥልጣን/ Bond Authority እጅ ይቆያል። ስለዚህ አዲሱ ባለንብረት ማስያዣው እንዲሰጠው ማመልከት ወይም ለርስዎ እንዲሰጥ ሊያቀናጅ ይችላል።

 ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

ማስያዣ ገንዘብ
ኮንትራትን ስለማቋረጥ
የማካካሻ ክፍያ ስለመጠየቅ
ስለ ባለንብረቶች ወይም ንብረት ተወካዮች ቅሬታዎች
ከቤት ማስወጣት
ከቤት ለመልቀቅ ማስጠንቀቂያ
ለብቻነት

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


The landlord is selling | Amharic | July 2013

እኛን ያግኙን

ለተከራዮች ምክር (advice for tenants)
እኛን ያግኙን (contact us)

የቪክቶርያ ተከረዮች | የተከራዮች የድጋፍ መስመር 03 9416 2577 | tuv.org.au
የቪክቶርያ ተከራዮች የቪክተርያ መንግስት ድጋፍ ዕውቅና ይሰጡታል፡፡

Tenants Victoria acknowledges the support of the Victorian Government.