የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ስለመጀመር - Tenants Victoria

የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ስለመጀመር

የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል (አንዳንዴ‘ኮንትራት/ lease’ ይባላል) በጽሁፍ ወይም በቃል ያለጽሁፍ ሊሆን እንደሚችልና ለተወሰነ የጊዜ ገደብ ሊሆን ይችላል (ለምሳሌ፡ ለ6 ወይም 12 ወራት) ወይንም በየጊዜው (ብዙጊዜ በየወሩ) የሚካሄድ ውል ሊሆን ይችላል።

ለተወሰነ ጊዜ ገደብ የሚቆይ ስምምነት ውል ደህንነቱ የበለጠ ይሆናል ምክንያቱም ባለንብረቱ ከቤት ሊያስወጣዎ ከበድ ስለሚለው፤ ነገር ግን ከተወሰነው ጊዜ ገደብ በፊት ቤቱን መልቀቅ ከፈለጉ ውድ ሊሆን ይችላል። በተወሰነ ጊዜ ገደብ ስምምነት ውል ላይ ለመቆየት እርግጠኛ ከሆኑ ብቻ ነው ለማይቀየር የተወሰነ ጊዜ ኮንትራት ውል ማካሄድ ያለብዎት።

ይህ ገጽ

የንብረት ሁኔታ መግለጫ ሪፖርት እና ሌላ ሰነዶች
የቤት ኪራይና ማስያዣ ገንዘብ

ገንዘብ ከፍለው ወደ ቤቱ ከመግባትዎ በፊት በንብረት ይዘት ሁኔታው ላይ ደስተኛ ስለመሆንዎ ማረጋገጥ። ባለንብረቱ ከመግባትዎ በፊት ቤቱን ለማስጠገን ወይም ለማሻሻል ቃል ከገባ (ለምሳሌ፡ ማሞቂያ ለማስገባት) ታዲያ በተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ውስጥ መካተቱን ወይም ቃል የገባበትን በጽሁፍ ተደርጎ ስለማግኘትዎ ማረጋገጥ።

በጽሁፍ የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ካለ እና ከመፈረምዎ በፊት አንድ ቅጂ ለርስዎ መሰጠት አለበት። በተለይ ‘ተጨማሪ የጊዜ ገደብ’ አብሮ ከተያያዘና አስፈላጊ ከሆነም ከመፈረምዎ በፊት ምክር ማግኘት። የስምምነት ውሉን ሲፈረሙ በ14 ቀናት ውስጥ ቅጂው ለርስዎ መሰጠት አለበት።

የንብረት ሁኔታ መግለጫ ሪፖርት እና ሌላ ሰነዶች

የርስዎ ተከራይና አከራይ ስምምነት ውል ሲጀምር ባለንብረቱ ለርስዎ መስጠት ያለበት:

  • የመብቶችና ግዲታዎች ጽሁፋዊ መግለጫ (ከConsumer Affairs Victoria ትንሽ መጽሐፍ)
  • የማስያዣ ገንዘብ ከከፈሉ፣ የተሞላ ንብረት መግለጫ ሪፖርት 2 ቅጂ እና በባለንብረቱ ወይም በተወካዩ የተፈረመበት
  • የባለንብረቱ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ተለፎን እና ፋክስ ቁጥር እንዲሁም ለአስቸኳይ ጥገና የንብረት ተወካዩ ስልጣን ካለው ወይም ከሌለው ጽሁፋዊ መግለጫ
  • የንብረት ተወካዩ በአስቸኳይ ጥገና ላይ ለማካሄድ ሥልጣን ካለው፤ ለጥገናው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጡና ለአስቸኳይ ጥገና ለማነጋገር የተወካዩን ተለፎን ወይም ፋክስ ቁጥር

በቤቱ በሚገቡበት ጊዜ ስለቤቱ ይዘት ሁኔታ ማስረጃ (በውስጥና በውጭ) የንብረት መግለጫ ሪፖርቱ ሊያካትት ይችላል። ሪፖርቱ ለማስያዣ ገንዘቡ መከራከሪያ ሊረዳ ሲችል ወይም የተከራይና አከራይ ስምምነት ውል በሚያልቅበት ጊዜ ለተበላሸ ወይም ለጽዳት የወጣን ወጪ ማካካሻ ገንዘብ ለመጠየቅ ይረዳል። በሁለቱም ሪፖርት ቅጂዎች ላይ ማንኛውንም ችግር መጠቀሱን ያረጋግጡ (እንደ ምንጣፍ ፍንጣቂ እድፍ)። በቅጹ ላይ በቂ ቦታ ከሌለ አስፈላጊ ከሆነ ክፍል ላይ ‘የተያያዘን ይመልከቱ’ በሚለው የተለየ ወረቀት ላይ ጽፎ ማያያዝ። ከተሞላ በኋላ በመፈረም አንዱን ቅጂ ለባለንብረቱ እና ሌላውን ደግሞ በጥሩ ቦታ ላይ ማስቀመጥ ነው። የንብረት መግለጫ ሪፖርቱን መሙላት፣ መፈረምና ወደ ቤቱ እንደገቡ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ መመለስ አለብዎ።

የቤት ኪራይና ማስያዣ ገንዘብ

የቤት ኪራይዎ በሳምንት $350 ዶላር ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ የአንድ ወር የቤት ኪራይ በቅድሚያ እዲከፍሉ ሲጠየቁ፤ በተጨማሪም የአንድ ወር የቤት ኪራይ በከፍተኛ መጠን ለማስያዣ ይጠየቃሉ። የቤት ኪራዩ በየሳምንቱ የሚከፈል ከሆነ የሁለት ሳምንት የቤት ኪራይ መጠን ብቻ በቅድሚያ ሊጠየቁ ይችላሉ።

የቤት ኪራይዎ በሳምንት ከ$350 ዶላር በላይ ከሆነ፤ በማስያዣ ገንዘቡ ወይም በቅድሚያ የቤት ኪራይ ላይ ከፍተኛ የመጠን ገደብ የለውም።

የሚከራየው ቤት የባለንብረቱ ዋና መኖሪያ ቦታ ስለመሆኑ በተከራይና አከራይ ኮንትራት ውሉ ላይ ተገልጾ ከሆነና ታዲያ የኮንትራቱ ሊዝ ሲያበቃ ወደ ቤቱ መመለስ ከፈለጉ፤ ከፍተኛ መጠን የማስያዣ ገንዘብ ገደብ አይኖርም።

የንብረት ተወካዮች (ወይም በዚህ ተሳታፊ የሆነ) ለመጀመሪያ ጊዜ በቤት ኪራይ ክፍያ በኩል ማስከፈል ወይም የቤት ኪራይ ክፍያን በቀጥታ ከተቀማጭ ገንዘብ በመቁረጥ መጠቀም ህገ-ወጥነት ነው።

የቤት ኪራይዎን በአካል ሂደው ከከፈሉ ወዲያውኑ ደረሰኝ ይሰጥዎታል። የቤት ኪራይዎን ለመክፈል ሌላ ዘዴ ከተጠቀሙ እና ክፍያውን በሚያካሂዱበት ጊዜ ደረሰኝ መጠየቅ ታዲያ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ደረሰኝ ለርስዎ መሰጠት አለበት። ምንም እንኳን በሚከፍሉበት ጊዜ ደረሰኝ ባይጠይቁም ነገር ግን በ12 ወራት ውስጥ ስለከፈሉት የቤት ኪራይ ሪኮርድ መዝገብ መጠየቅ እንደሚችሉ ነው። ላካሄዱት ክፍያዎች የቅጂ ምዝገባ ሪኮርድ ሲጠይቁ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለርስዎ መሰጠት አለበት።

በአብዛኛው ሁለቱን ማለት ለማስያዣና ለዋስትና የሚሆን ገንዘብ መጠየቅ አይችሉም። ከተጠየቁም ምክር ለማግኘት የTenants Union/Tenants Victoria ን ያነጋግሩ።

የማስያዣ ገንዘብዎን ሲከፍሉ ባለንብረቱ ወይም ተወካዩ የማስያዣ ገንዘብ ማስገቢያ ቅጹን መሙላትና መፈረም እንዳለበትና በቅጹ ላይ እንዲፈርሙ ይሰጥዎታል። የርስዎን ማስያዣ ገንዘብና ቅጹን በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ Residential Tenancies Bond Authority ማስገባት አለባቸው። በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ የማስያዣ ገንዘብ ባለሥልጣን ስለመድረሱ ለርስዎ ደረሰኝ መላክ አለበት።

 ይህ መረጃ ለመመሪያ ብቻ እንዲሆን እንጂ የህግ ባለሞያ ምክርን ተክቶ መጠቀም ኣይቻልም።

ከዚህ ጋር የተዛመዱ ገጾች

የግል መኖሪያ ቤት ኪራይ ስለማመልከት

ማስያዣ ገንዘብ

ኮንትራትን ስለማቋረጥ

ስለ ባለንብረቶች ወይም ንብረት ተወካዮች ቅሬታዎች

የቤት ኪራይ ስለመጨመር

በበለጠ እርዳታ ይፈለጋልን?

ተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ካስፈለግዎት እባክዎ እኛን ያነጋግሩ።


Starting a tenancy | Amharic | June 2012

እኛን ያግኙን

ለተከራዮች ምክር (advice for tenants)
እኛን ያግኙን (contact us)

የቪክቶርያ ተከረዮች | የተከራዮች የድጋፍ መስመር 03 9416 2577 | tuv.org.au
የቪክቶርያ ተከራዮች የቪክተርያ መንግስት ድጋፍ ዕውቅና ይሰጡታል፡፡

Tenants Victoria acknowledges the support of the Victorian Government.